የዲሲ የህዝብ ቤተ መፃህፍት የሼፐርድ ፓርክ ቤተ መፃህፍት ወደ አዲሱ የዋልተር ሪድ ልማት (በሰሜን በፈርን ስትሪት እና በደቡብ በአስፐን ስትሪት የሚዋሰን) ቦታ ለመቀየር በታሰበው ሁኔታ ላይ የማህበረሰብ አስተያየት እየሰበሰበ ነው።
ይህ የዳሰሳ ጥናት ዓላማው በቤተ መፃህፍቱ ወደ ሌላ ቦታ መዛወር ዙሪያ የእርስዎን ሀሳብ እንዲሁም ከቤተ-መጽሐፍት አጠቃቀምዎ ጋር በተገናኘ ለእርስዎ በጣም አስፈላጊ የሆኑ እና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች ለመረዳት ነው። ቤተ መፃህፍቱን አሁን እንዴት ይጠቀማሉ? ለወደፊቱ ቤተ መፃህፍቱን እንዴት ለመጠቀም ያስባሉ? ቤተ መፃህፍቱ የሚገኝበት ቦታ የቤተመፃህፍቱን አገልግሎቶች ማግኘትዎ ላይ ምን ተጽእኖ አለው?
ይህን የዳሰሳ ጥናት ለማጠናቀቅ 6 ደቂቃ ያህል ይወስዳል። ሀሳብዎን ስላጋሩን እናመሰግናለን!